የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ ለኤች አይ ቪ ኘሮግራም ማስፈፀሚያ አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችና ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል::
Contact
www.extratenders.net
Posted Date/የተለጠፈበት ቀን
Jan-25-23 13:51:33
Tender detail Information /ዝርዝር መረጃ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ ለኤች አይ ቪ ኘሮግራም ማስፈፀሚያ አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችና ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል:: ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል::
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው::
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ሰርተፍኬት/ የሚያቀርቡ::
- ከላይ በተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ የሚችሉ::
- የሚገዛው ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ ከ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የቫት ሰርተፊኬት ኮፒ ማስያዝ አለባቸው::
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩት ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የሚያስይዙ::
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳቡን በታሸገ ፖስታ ጤና ጥበቃ ቢሮ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ግዥ ክፍል ጃይካ ህንፃ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት በ15 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግዥ ክፍል/በቢሮ በ16ኛዉ ቀን 2015 ዓ.ም በ 8:30 ታሽጎ 9፡00 ይከፈታል:: ሆኖም ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በተከታዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል::
- ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም::
- ቢሮው የግዥዉን መጠን እስከ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል::
- የጨረታዉ አሸናፊ የሆነ ድርጅት ለማቅረብ ያሸነፈውን ተሸከርካሪ ከአሽከርካሪው /ከሹፌሩ/ ጋር ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ድረስ ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት ቀናት አስከ 11፡30 እና በአስራ ስድስተኛው ቀን እስከ 8.፡30 ድረስ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 213 ድረስ በአካል ቀርቦ የጨረታ ሰነዱን በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ::
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ስለ ጨረታዉ መረጃ ከፈለጉ አብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ ቁጥር-ጃይካ ህንፃ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582221127 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል::
አብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ ባህር ዳር
Source ባህር ዳር በኩር ጥር 15/2015
Specific details
Advert Location
Amhara Region
ስልክ ቁጥር 0582221127 አብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ ባህር ዳር
ስልክ ቁጥር 0582221127 አብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ ባህር ዳር
Advert details
Advert ID:
79334
Viewed :
10
Modified:
Jan-25-23 13:51:33
Expires/መዝጊያ ቀን:
Feb-06-23 13:51:33
In categories:
Bekur (Bahir Dar ) Tenders