በምዕ/ጐጃም ዞን የአዴት ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2014 በጀት ዓመት ስራ ላይ የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች እና መገጣጠሚያዎች በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Add to Favourites
Send me via
Contact ስልክ ቁጥር 0985895037/0583380793
Posted Date/የተለጠፈበት ቀን Sep-15-21 16:39:26

Tender detail Information /ዝርዝር መረጃ

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በምዕ/ጐጃም ዞን የአዴት ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2014 በጀት ዓመት ስራ ላይ የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች እና መገጣጠሚያዎች በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ

የሚከተሉትን መስፈርቶች ያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ጨረታውም በሎት የሚታይ ይሆናል፡፡ ሎት 1 ፊቲንግ/መገጣጠሚያ ፣ ሎት እስቴሽነሪ/አላቂ እቃዎች/ ሎት 3 የኤሌክትሪክ እቃዎች በዚህ መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተጫራች መወዳደር የሚችል መሆኑን ይገልፃል፡፡

  1. በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያለው እና የ2013 አመተ ምህረት ግብር ከፍሎ ፈቃድ ያሣደሰ እና እቃው 50 ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑትን የሚያሣትፍ ይሆናል፡፡
  2. የግብር ከፋይ ለመሆኑ መለያ ቁጥር/የምስክር ወረቀት/ አብሮ ማስያዝ አለበት፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ሂሣብ ሲፒኦ/በጥሬ ገንዘብ/ የጠቅላላውን ዋጋ 1 በመቶ ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡
  4. ተጫራቹ ዋጋ ሲሞሉ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቹ ዋጋ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ፡፡
  6. ተጫራቹ ድርጅት እቃውን በተጠየቀው ስፔስፊኬሽን እና ጽ/ቤቱ ውስጥ ባሉ ሣምፕሎች መሰረት ማቅረብ የሚችል፡፡
  7. በሌላ ተጫራች ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  8. ተጫራቹ ዋጋ መሙያ የራሱ ማህተም፣ ስም፣ ፊርማ ስልክ ቁጥር ማስቀመጥ አለበት፡፡
  9. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30 ቀናት በአየር ላይ ይቆያል፡፡ በዚሁ ቀን 5፡30 ድረስ የጨረታ ሣጥኑ ክፍት ሆኖ በ6፡00 የጨረታ ሣጥኑ ይታሸጋል፡፡ በ7፡30 ላይ ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት ጽ/ቤቱ ወደ ኋላ አይልም፡፡ የጨረታ መክፈቻ የበዓል ቀን ከሆነ ያንኑ ሰዓት ጠብቆ በቀጣዩ ቀን ይከፈታል፡፡

10.መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ይህም

ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ምክንያት ተጫራቾች ላወጡት ማንኛውም ወጭ ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን

የማይወስድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

11.ተጫራቾች የበለጠ ለመረዳት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0985895037/0583380793 ደውለውማረጋገጥ ይችላሉ፡፡

12.የጨረታ ሰነዱን ከወጣበት ቀን ጀምሮ በዘርፉ የሚመለከታቸው ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 ከፍሎ ቢሮ ቁጥር 1 መግዛት ይችላሉ፡፡

13.አሸናፊው ድርጅት እቃውን አዴት ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ሊያቀርብ ነው፡፡

14.የሚገዙ የእቃዎች ዓይነት ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሸን/ ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያይዟል፡፡ ሣፕል ከጽ/ቤት ማየት ይቻላል፡፡ የሚቀርቡ እቃዎች በእኛ የጥራት ኮሚቴ እቃው ታይቶ ጥራቱ ዝቅተኛ ከሆነ/ጥራት ከሌላቸው/ ጽ/ቤቱ የማይረከብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የአዴት ከተማ ውሃ አገልግሎት /ቤት

Source ባህር ዳር በኩር መስከረም 3/01/2014

Specific details

Tenders Type Local Tenders
Data Source Bekur Gazita
Tenders Language Am..........show
CPO / ቢድ ቦንድ ( % or Flat Fee) 1%

Advert Location

Amhara Region
ስልክ ቁጥር 0985895037/0583380793

Advert details

Advert ID: 43106
Viewed : 7
Expires/መዝጊያ ቀን: Oct-12-21 16:36:00